Pixlr Editor
ID
icmaknaampgiegkcjlimdiidlhopknpkPixlr Editor ሁሉንም የአርትዖት ፍላጎቶችዎን የሚያሟላ በአሳሽ ውስጥ የሚሠራ የፎቶ አርታዒ ነው። ንብርብሮችን እና ውጤቶችን ጨምሮ ምስሎችዎን ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠሩ።
ቅጽበታዊ ገጽ እይታዎች
መግለጫ
Pixlr Editor ሁሉንም የአርትዖት ፍላጎቶችዎን የሚያሟላ በአሳሽ ውስጥ የሚሠራ የፎቶ አርታዒ ነው። ንብርብሮችን እና ውጤቶችን ጨምሮ ምስሎችዎን ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠሩ።
Pixlr Editor ከፍተኛ ችሎታ ካላቸው የመስመር ላይ የፎቶ አርታዒዎች መካከል እጅግ ተወዳጁ ነው። ማውረድ አያስፈልግም፣ እና 100% ነፃ ነው።
በGimp፣ PaintShop Pro ወይም Photoshop መሥራት ከለመዱ፣ ይህን የመስመር ላይ የምስል አርታዒ መጠቀም የተለመደ ይመስልዎታል። በኮምፒውተር ላይ በሚጫኑ የግራፊክ ዲዛይን መተግበሪያዎች ውስጥ በተለምዶ የሚያዩዋቸውን ብዙ ባህሪያት ይዟል። መመዝገብ ሳያስፈልግዎ ወዲያውኑ ይህን መሣሪያ መጠቀም ይጀምሩ።
• መለያ አያስፈልግም። ከፈለጉ ነፃ የማከማቻ ቦታ ለማግኘት መለያ ይፍጠሩ።
• ልዩ ነገር ማውረድ ወይም መጫን አያስፈልግም። በሚፈልጉበት ጊዜ በአሳሽዎ ውስጥ ብቻ ይክፈቱት።
• እንደ ንብርብሮች፣ በነፃ ቅርጽ የመምረጫ መሣሪያ፣ የብሩሽ መቆጣጠሪያዎች፣ ከምስሉ ክፍል በመቅዳት ሌላ ክፍል የመሙያ እና ማጣሪያዎች ያሉ መሣሪያዎችን ያቀርባል።
• ሁሉንም ፎቶዎችዎን እና ምስሎችዎን ማከማቸት የሚችሉበት የግል Pixlr Library በምርጫ ይቀርባል።
መሣሪያዎቹ የቀይ ዓይን ተጽዕኖን መቀነስ፣ የነጠብጣብ ማስወገጃ፣ የስዕል መሣሪያዎች፣ የምስል ክፍል መቅጃ መሣሪያዎች፣ ማጥራት፣ ማደብዘዝ እና ሌሎች ብዙ ነገሮችን ያካትታሉ።
ማጣሪያዎቹ HDRን መምሰል፣ የውበት ፍካት፣ የማዘንበልና የማንሸራተት ውጤት፣ ጋውሲያን ማደብዘዝ፣ ጠርዞችን ማጨለም፣ የምስል ነጠብጣቦች እና ሌሎች ብዙ ውጤቶችን ያካትታሉ።
ማስተካከያዎቹ እንደ የብርሃን ደረጃዎች፣ ኩርባዎች፣ የተሻጋሪ ማቀነባበር የቀለም ውጤት፣ የቀለም ሙሌትን ማስወገድ፣ ራስ-ሰር የብርሃን ደረጃዎች፣ የቀለም አይነት/ሙሌት እና ብሩህነት/ንፅፅር ያሉ የላቁ ጽንሰ ሐሳቦችን ያካትታሉ።